ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 2:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ ደስም ይበልሽ፤ እኔ እመጣለሁና፤ በመካከልሽም እኖራለሁ” ይላል እግዚአብሔር።

11. “በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት ወደ አንቺ እንደ ላከኝም ታውቃላችሁ።

12. እግዚአብሔርም በተቀደሰችው ምድር ይሁዳን ርስቱ አድርጎ ይወርሳል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደ ገና ይመርጣል።

13. እግዚአብሔር ከተቀደሰ ማደሪያው ተነሥቶአልና፣ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሆይ፤ በፊቱ ጸጥ በል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 2