ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘካርያስ 13:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. አንድ ሰው፣ ‘ይህ በሰውነትህ ላይ ያለው ቊስል ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቀው፣ ‘በባልንጀሮቼ ቤት ሳለሁ የቈሰልሁት ነው’ ይላል።

7. እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤“ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ!እረኛውን ምታ፤በጎቹ ይበተናሉ፤እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።

8. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የምድር ሁሉ፣ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤አንድ ሦስተኛው ግን በውስጡ ይቀራል፤

9. ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤እኔም እመልስላቸዋለሁ፤እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘካርያስ 13