ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 5:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. “ ‘ካህኑ እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጻፍ፤ በመራራውም ውሃ ይደምስሳቸው።

24. ርግማን የሚያመጣውንም ውሃ ሴትየዋ እንድትጠጣ ያድርግ፤ ውሃውም ወደ ሰውነቷ ገብቶ የመረረ ሥቃይ ያስከትልባታል።

25. ካህኑ ለቅናት የቀረበውን የእህል ቊርባን ይቀበላት፤ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወዝውዞ ወደ መሠዊያው ያቅርበው።

26. ካህኑ የመታሰቢያ ቊርባን እንዲሆን እፍኝ የእህል ቍርባን ከዚያ ወስዶ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ከዚያም በኋላ ሴቲቱ ውሃውን እንድትጠጣ ያድርግ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 5