ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 33:40-54 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

40. በከነዓን በምትገኘው በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ፣ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ።

41. እነርሱም ከሖር ተራራ ተነሥተው በሴልሞና ሰፈሩ።

42. ከሴልሞና ተነሥተው በፋኖን ሰፈሩ።

43. ከፋኖን ተነሥተው በአቦት ሰፈሩ።

44. ከአቦት ተነሥተው በሞዓብ ዳርቻ በምትገኘው በኢየአባሪም ሰፈሩ።

45. ከኢይም ተነሥተው በዲቦንጋድ ሰፈሩ።

46. ከዲቦንጋድ ተነሥተው በዓልሞን ዲብላታይም ሰፈሩ።

47. ከዓልሞንዲብላታይም ተነሥተው በናባው አጠገብ በሚገኙት በዓብሪም ተራራዎች ላይ ሰፈሩ።

48. ከዓብሪም ተራራዎች ተነሥተው ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ።

49. እዚያም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ከቤት የሺሞት እስከ አቤልስጢም ባለው ስፍራ ሰፈሩ።

50. ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

51. “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ወደ ከነዓን ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ፣

52. የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አሳዳችሁ አስወጧቸው፤ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶቻቸውን በሙሉ አጥፉ፤ እንዲሁም በኰረብታ ላይ የተሠሩትን መስገጃዎቻቸውን ሁሉ አፈራርሱ።

53. ምድሪቱን ርስት አድርጌ ሰጥቻችኋለሁና ውረሷት፤ ኑሩባትም።

54. ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቊጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቊጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 33