ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 3:47-51 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

47. ለእያንዳንዱ በኵር ክብደቱ ባለ ሃያ አቦሊ በሆነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ልክ አምስት አምስት ሰቅል ተቀበል፤

48. የተረፉትንም እስራኤላውያን ለመዋጀት ገንዘቡን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ።”

49. ስለዚህ ሙሴ በሌዋውያኑ ተዋጅተው ቍጥራቸው ትርፍ ከሆነው በኵሮች ላይ የመዋጃውን ገንዘብ ተቀበለ፤

50. ከእስራኤላውያን በኵሮች ላይ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ አንድ ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ሰቅል ሰበሰበ።

51. ሙሴም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ቃል በታዘዘው መሠረት የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጣቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 3