ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 3:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን በሲና ምድረ በዳ፣

15. “ሌዋውያንን በየቤታቸውና በየጐሣቸው ቍጠር፤ የምትቈጥረውም አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ ነው” አለው።

16. ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ቃል በታዘዘው መሠረት እነዚህን ቈጠራቸው።

17. የሌዊ ልጆች ስምጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነው።

18. የጌድሶን ልጆች ጐሣ ስምሎቢኒና ሰሜኢ ነው።

19. የቀዓት ጐሣዎች፤እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮን፣ ዑዝኤል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 3