ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 29:26-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. “ ‘በአምስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዘጠኝ ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

27. ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

28. ደግሞም ከእህሉ ቊርባኑና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

29. “ ‘በስድስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

30. ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

31. ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

32. “ ‘በሰባተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ሰባት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።

33. ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቊጥር መሠረት አቅርቡ።

34. ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቊርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

35. “ ‘በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራም አትሥሩ።

36. ሁሉም እንከን የሌለባቸው አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግና ዓመት የሆናቸው ሰባት ተባዕት የበግ ጠቦቶች የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ቍርባን በእሳት አቅርቡ።

37. ከወይፈኑ፣ ከአውራ በጉና ከበግ ጠቦቶቹ ጋር የእህል ቊርባናቸውንና የመጠጥ ቊርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።

38. ደግሞም ከእህሉ ቊርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋር በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

39. በስእለትና በበጎ ፈቃድ ከምታቀርቧቸው ቍርባኖች በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቊርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቊርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በተወሰኑት በዓሎቻችሁ ላይ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) አቅርቡ።’ ”

40. ሙሴም እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ሁሉ ለእስራኤላውያን ነገራቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 29