ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 26:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።

8. የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣

9. የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።

10. ሁለት መቶ አምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከእርሱ ጋር ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤

11. የቆሬ የዘር ሐረግ ግን አልጠፋም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 26