ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 15:28-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. ከዚያም ካህኑ፣ ባለማወቅ ኀጢአት ሠርቶ ለተሣሣተው ሰው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ያስተሰርይለታል፤ ስርየት በሚደረግለትም ጊዜ ሰውየው ይቅር ይባላል።

29. ያገር ተወላጅ እስራኤላዊ ይሁን ወይም መጻተኛ ባለማወቅ ኀጢአት ከሠራ በማናቸውም ሰው ላይ ሕጉ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።

30. “ ‘ያገር ተወላጅም ይሁን መጻተኛ ሆን ብሎ ኀጢአት የሚሠራ ማንኛውም ሰው ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ) ስለሚያቃልል ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።

31. የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቃል ስለናቀ፣ ትእዛዛቱንም ስለ ጣሰ ያ ሰው በእርግጥ ተለይቶ መጥፋት አለበት፤ ጥፋቱ የራሱ ነው።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 15