ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 13:9-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ከብንያም ነገድ፣ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤

10. ከዛብሎን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፤

11. ከምናሴ ነገድ ይህም የዮሴፍ ነገድነው፤ የሱሲ ልጅ ጋዲ፤

12. ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤

13. ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤

14. ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፤

15. ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል።

16. እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት።

17. ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ነጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ።

18. ምድሪቱ ምን እንደምትመስልና የሚኖሩባትም ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፣ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች መሆናቸውን እዩ።

19. የሚኖሩባት ምድር ምን ዐይነት ናት? መልካም ወይስ መጥፎ? የሚኖሩባቸውስ ከተሞች ምን ይመስላሉ? በግንብ ያልታጠሩ ናቸው ወይስ የተመሸጉ?

20. ዐፈሩስ እንዴት ያለ ነው? ለም ወይስ ደረቅ? ደናም ወይስ ደን አልባ? በተቻለ መጠን ከምድሪቱ ፍሬ ይዛችሁ ኑ። ወቅቱ የወይን ፍሬ መብሰል የጀመረበት ጊዜ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 13