ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 13:31-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. ከእነርሱ ጋር የወጡት ሰዎች ግን፣ “ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለሆኑ፣ ልናሸንፋቸው አንችልም” አሉ።

32. እነዚህም ስለ ሰለሏት ምድር በእስራኤላውያን መካከል እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አሠራጩ፤ “ያየናት ምድር የሚኖሩባትን ሰዎች የምትበላ ናት፤ እዚያ ያየናቸው ሰዎች ሁሉ ግዙፎች ናቸው፤

33. ኔፊሊምንም በዚያ አይተናል፤ የዔናቅ ዝርያዎች የመጡት ከኔፊሊም ነው። ራሳችንን ስናየው እንደ አንበጣ ነበርን፤ በእነርሱ ዐይን የታየነውም በዚሁ መልክ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 13