ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 1:2-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “የወንዶቹን ስም አንድ በአንድ በመዘርዘር መላውን የእስራኤል ማኅበረሰብ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቍጠሯቸው።

3. በመላው እስራኤል ያሉትን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያም በላይ ሆኖ ለውጊያ ብቁ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንተና አሮን በየምድባቸው ቍጠሯቸው።

4. ከየነገዱ የአባቶች ቤት ተጠሪ የሆነ አንድ ሰው ከእናንተ ጋር ይሁን።

5. የሚረዷችሁም ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፦“ከሮቤል የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፤

6. ከስምዖን የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤

7. ከይሁዳ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤

8. ከይሳኮር የሶገር ልጅ ናትናኤል፤

9. ከዛብሎን የኬሎን ልጅ ኤልያብ፤

10. ከዮሴፍ ልጆች ከኤፍሬም የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፤ከምናሴ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል

11. ከብንያም የጋዴዮን ልጅ አቢዳን፤

12. ከዳን የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር፤

13. ከአሴር የኤክራን ልጅ ፋግኤል፤

14. ከጋድ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ፤

15. ከንፍታሌም የዔናን ልጅ አኪሬ።”

16. እነዚህ ከማኅበረ ሰቡ የተመረጡ የየነገዱ አለቆች ሲሆኑ እነርሱም የእስራኤል ጐሣዎች መሪዎች ነበሩ።

17. ሙሴና አሮን ስማቸው የተጠቀሰውን እነዚህን ሰዎች ወሰዱ፤

18. ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 1