ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 1:19-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜአቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነ ወንዶች ስማቸው አንድ በአንድ ተመዘገበ። እንዲህ አድርጎም በሲና ምድረ በዳ ቈጠራቸው።

20. ከእስራኤል የበኵር ልጅ ከሮቤል ዝርያ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኖ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

21. ከሮቤል ነገድ የተቈጠሩት አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

22. ከስምዖን ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

23. ከስምዖን ነገድ የተቈጠሩት አምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።

24. ከጋድ ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

25. ከጋድ ነገድ የተቈጠሩትም አርባ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አምሳ ነበሩ።

26. ከይሁዳ ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

27. ከይሁዳ ነገድ የተቈጠሩትም ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።

28. ከይሳኮር ዝርያ፦ዕድሜአቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

29. ከይሳኮር ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

30. ከዛብሎን ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ አመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

31. ከዛብሎን ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 1