ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘኁልቍ 1:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን በሲና ምድረ በዳ ሳሉ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ተናገረው፤ እንዲህም አለው፤

2. “የወንዶቹን ስም አንድ በአንድ በመዘርዘር መላውን የእስራኤል ማኅበረሰብ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቍጠሯቸው።

3. በመላው እስራኤል ያሉትን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያም በላይ ሆኖ ለውጊያ ብቁ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንተና አሮን በየምድባቸው ቍጠሯቸው።

4. ከየነገዱ የአባቶች ቤት ተጠሪ የሆነ አንድ ሰው ከእናንተ ጋር ይሁን።

5. የሚረዷችሁም ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፦“ከሮቤል የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፤

6. ከስምዖን የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘኁልቍ 1