ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 21:21-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጒድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ለማቅረብ አይምጣ።

22. እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን (ኤሎሂም) ምግብ ይብላ።

23. ነገር ግን እንከን ያለበት ስለ ሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

24. ሙሴም ይህን ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን ሁሉ ነገራቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 21