ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 17:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

2. “ለአሮንና ለልጆቹ፣ ለእስራኤላውያንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘው ይህ ነው፤

3. ማንኛውም እስራኤላዊ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ ወይም ፍየል ቢያርድ፣

4. በእግዚአብሔር (ያህዌ) ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፣ ያ ሰው በከንቱ ደም እንዳፈሰሰ ይቈጠራል፤ ደም በማፍሰሱም ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።

5. እስራኤላውያን የሚሠዉትን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያመጡበት ምክንያት ከዚሁ የተነሣ ነው። ይህንም ካህኑ ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥተው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኅብረት መሥዋዕት በማድረግ ያቅርቡ።

6. ካህኑም ደሙን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር (ያህዌ) መሠዊያ ላይ ይርጭ፤ ሥቡንም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ሽታ እንዲሆን ያቃጥል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 17