ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 17:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

2. “ለአሮንና ለልጆቹ፣ ለእስራኤላውያንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘው ይህ ነው፤

3. ማንኛውም እስራኤላዊ በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ ወይም ፍየል ቢያርድ፣

4. በእግዚአብሔር (ያህዌ) ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፣ ያ ሰው በከንቱ ደም እንዳፈሰሰ ይቈጠራል፤ ደም በማፍሰሱም ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 17