ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዘሌዋውያን 15:5-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ዐልጋውን የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

6. ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው በተቀመጠበት በየትኛውም ነገር ላይ የተቀመጠ ሰው ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

7. “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣውን ሰው የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

8. “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው ንጹሕ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ፣ የተተፋበት ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

9. “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው የተቀመጠበት ኮርቻ ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤

10. ከበታቹ ያለውንም ነገር ሁሉ የነካ ማንም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

11. “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው እጁን በውሃ ሳይታጠብ ሌላውን ሰው ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

12. “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው የነካው የሸክላ ዕቃ ይሰበር፤ ከዕንጨት የተሠራ ዕቃ ከሆነ በውሃ ይታጠብ።

13. “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ፣ በሕጉ መሠረት ለመንጻቱ ሰባት ቀን ይቊጠር፤ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በምንጭ ውሃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።

14. በስምንተኛውም ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት የዋኖስ ጫጩቶች ይዞ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በመቅረብ ለካህኑ ይስጥ።

15. ካህኑም አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መሠረት ስለ ፈሳሹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለሰውየው ያስተሰርይለታል።

16. “ ‘አንድ ሰው ዘሩ በሚፈስበት ጊዜ ሰውነቱን በሙሉ በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

17. የፈሰሰው ዘር የነካው ማንኛውም ልብስ ወይም ቊርበት በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል።

18. አንድ ሰው ከአንዲት ሴት ጋር ግብረ ሥጋ ፈጽሞ ዘር ቢፈሰው፣ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩሳን ይሆናሉ።

19. “ ‘ሴት ጊዜውን እየጠበቀ የሚመጣው የደም መፍሰስ ቢኖርባት፣ የወር አበባዋ ርኵሰት እስከ ሰባት ቀን ይቆያል፤ በዚህ ጊዜ ማንም ሰው ቢነካት እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዘሌዋውያን 15