ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 8:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. “እንዲህ በላቸው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ሰዎች ቢውድቁ፣ እንደ ገና ከወደቁበት አይነሡምን?ሰው ተሳስቶ ወደ ኋላ ቢሄድ፣ ከስሕተቱ አይመለስምን?

5. ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል?ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች?ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።

6. እኔ በጥንቃቄ አደመጥኋቸው፤ትክክለኛ የሆነውን ግን አይናገሩም።ማንም ስለ ክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤“ምን አድርጌአለሁ?” ይላል።ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ፈረስ፣እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይሄዳል።

7. ሽመላ እንኳ በሰማይ፣የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፣ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም፣የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤ሕዝቤ ግን፣ የእግዚአብሔርን ሥርዐት አላወቀም።

8. “ ‘የጸሓፊዎቻችሁ ሐሰተኛ ብርዕ ሐሰትእያስተናገደ እንዴት፣ “ዐዋቂዎች ነን፣ የእግዚአብሔር ሕግ አለን” ትላላችሁ?

9. ጥበበኞች ያፍራሉ፤ይዋረዳሉ፤ በወጥመድም ይያዛሉ። የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው፣ምን ዐይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?

10. ስለዚህ ሚስቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ፤ዕርሻዎቻቸውንም ለባዕዳን እሰጣለሁ፤ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ፣ሁሉም ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ይስገበገባሉ፤ነቢያትና ካህናትም እንዲሁ፤ሁሉም ያጭበረብራሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 8