ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 5:27-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ወፎች እንደሞሉት ጐጆ፣ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤

28. ወፍረዋል፤ ሰብተዋልም።ክፋታቸው ገደብ የለውም፤ወላጅ የሌላቸው ፍትሕ እንዲያገኙአልቆሙላቸውም፤ለድኾችም መብት አልተከራከሩም።

29. ስለ እነዚህ ነገሮች ልቀጣቸው አይገባኝምን?”ይላል እግዚአብሔር።እንዲህ ዐይነቶቹን ሕዝብ፣እኔ ራሴ ልበቀላቸው አይገባኝምን?

30. “የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር፣በምድሪቱ ላይ ሆኖአል፤

31. ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ካህናት በነቢያቱ ምክር ያስተዳድራሉ፤ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ይወዳሉ፤ፍጻሜው ሲደርስ ግን ምን ታደርጉ ይሆን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 5