ሐሴቦን ሆይ፤ ጋይ ጠፍታለችና ዋይ በይ፤የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ ጩኹ፤ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ሚልኮም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣ተማርኮ ይወሰዳልና፣በቅጥር ውስጥ ወዲያ ወዲህ ተሯሯጡ።