ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 48:34-41 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. “ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤የኔሞሬም ውሃ እንኳ ደርቆአልና።

35. በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣ከሞዓብ አጠፋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

36. “ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል፤ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል።ያከማቹት ንብረት ጠፍቶአልና።

37. የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል፤እጅ ሁሉ ተቸፍችፎአል፤ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቆአል።

38. በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፤፣በሕዝብም አደባባዮች፣ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤እንደማይፈለግ እንስራ፣ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤”ይላል እግዚአብሔር።

39. “እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ!ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ!ሞዓብ የመሰደቢያ፣በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”

40. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።

41. ከተሞቹ ይወረራሉ፤ምሽጎቹም ይያዛሉ፤በዚያን ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 48