ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 48:32-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. የሴባማ ወይን ሆይ፤ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣አጥፊው መጥቶአል።

33. ከሞዓብ የአትክልት ቦታና እርሻ፣ሐሤትና ደስታ ርቆአል፤የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣የእልልታ ድምፅ አይደለም።

34. “ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤የኔሞሬም ውሃ እንኳ ደርቆአልና።

35. በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣ከሞዓብ አጠፋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

36. “ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል፤ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል።ያከማቹት ንብረት ጠፍቶአልና።

37. የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል፤እጅ ሁሉ ተቸፍችፎአል፤ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቆአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 48