ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 47:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ፈርዖን ጋዛን ድል ከማድረጉ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ በሰሜን በኩል ውሃ እየሞላ ነው፣ኀይለኛ ጐርፍ ይሆናል፤አገሪቷንና በውስጧ ያሉትንም ሁሉ፣ከተሞቿንና ነዋሪዎቻቸውን ያጥለቀልቃል።ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላል፤

3. ከፈረስ ኮቴ ድምፅ፣ከጠላት ሠረገላ ጩኸትና፣ከሠረገላው ሽክርክሪት ፍትጊያ ድምፅ የተነሣ፣አባቶች ልጆቻቸውን ለመርዳት ወደ ኋላ መለስ አይሉም፤እጃቸውም ስንኩል ይሆናል።

4. ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ቀኑ ደርሶአልና። እግዚአብሔር በከፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋተነሥቶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 47