ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 46:18-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሡ እንዲህ ይላል፤በሕያውነቴ እምላለሁ።በተራሮች መካከል ያለውን የታቦር ተራራ የሚመስል፣ባሕርም አጠገብ ያለውን የቀርሜሎስ ተራራ የሚመስል አንድ የሚመጣ አለ።

19. እናንተ በግብፅ የምትኖሩ ሆይ፤በምርኮ ለመወሰድ ጓዛችሁን አሰናዱ፤ሜምፎስ ፈራርሳ፣ሰው የማይኖርባት ባድማ ትሆናለችና።

20. “ግብፅ ያማረች ጊደር ናት፣ነገር ግን ተናዳፊ ዝንብ፣ከሰሜን ይመጣባታል።

21. ቅጥረኞች ወታደሮቿም፣እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፣በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።

22. ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣ግብፅ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል።

23. ጥቅጥቅ ጫካ ቢሆንም፣ ደን ይመነጥራሉ፤”ይላል እግዚአብሔር፤“ብዛታቸው እንደ አንበጣ ነው፤ሊቈጠሩም አይችሉም።

24. የግብፅ ሴት ልጅ ለኀፍረት ትጋለጣለች፤ለሰሜን ሕዝብም ዐልፋ ትሰጣለች።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 46