ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 4:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “እስራኤል ሆይ፤ ብትመለስ፣ወደ እኔ ብትመለስ፤”ይላል እግዚአብሔር፤“አስጸያፊ ነገሮችህን ከፊቴ ብታስወግድ፣ባትናወጥ ብትቆምም፣

2. በእውነት፣ በቅንነትና በጽድቅ፣‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብለህ ብትምል፣አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤በእርሱም ይከበራሉ።”

3. እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ያላል፤“ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤በእሾህም መካከል አትዝሩ።

4. እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ሊገታውም የሚችል የለም።

5. “ ‘በምድሪቱ ሁሉ መለከትን ንፉ’ ብላችሁ፤በይሁዳ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌም ዐውጁ፤ጩኹ፤ እንዲህም በሉ፤‘በአንድነት ተሰብሰቡ፤ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ’

6. ወደ ጽዮን ለመግባት ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ቶሎ ሸሽታችሁ አምልጡ፤ከሰሜን መቅሠፍትን፣ታላቅ ጥፋትን አመጣለሁና።”

7. አንበሳ ከደኑ ወጥቶአል፤ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቶአል፤ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ከስፍራው ወጥቶአል።ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 4