እናንተ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፤ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፤የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ፤አለዚያ ስለ ሠራችሁት ክፋት፣ቍጣዬ እንደ እሳት ይንበለበላል፤ሊገታውም የሚችል የለም።