ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 31:37-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በላይ ያሉትን ሰማያትን መለካት፣በታችም ያሉትን የምድር መሠረቶች መመርመር ከተቻለ፣በዚያ ጊዜ የእስራኤልን ዘር ሁሉ፣ስላደረጉት ነገር ሁሉ እጥላቸዋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

38. “እነሆ ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማእዘኑ በር ድረስ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ይህች ከተማ ለእግዚአብሔር የምትሠራበት ጊዜ ይመጣል፤

39. መለኪያ ገመዱም ከዚያ ጀምሮ በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኰረብታ፣ አልፎም ወደ ጎዓ ይዘረጋል።

40. ሬሳና ዐመድ የሚጣልበት ሸለቆ በሙሉ፣ በምሥራቅ በኩል የቄድሮንን ሸለቆ ይዞ እስከ ፈረስ በር የሚደርሰው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ከተማይቱ አትነቀልም፤ አትፈርስምም።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 31