ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 31:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “በዚያ ዘመን” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለእስራኤል ነገድ ሁሉ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”

2. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ፣በምድረ በዳ ሞገስን ያገኛል፤እኔም ለእስራኤል ዕረፍት ለመስጠት እመጣለሁ።”

3. እግዚአብሔር ከሩቅ ተገለጠልን፤ እንዲህም አለን፤“በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ስለዚህም በርኅራኄ ሳብሁሽ።

4. የእስራኤል ድንግል ሆይ፤ እንደ ገና አንጽሻለሁ፤አንቺም ትታነጪያለሽ፤ከበሮችሽንም እንደ ገና አንሥተሽ፣ከሚፈነጥዙት ጋር ትፈነድቂያለሽ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 31