ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 18:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማኝ፤ባላንጣዎቼ የሚሉትን አድምጥ።

20. የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን?እነርሱ ግን ጒድጓድ ቈፈሩልኝ፤ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣በፊትህ ቆሜ፣ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ አስብ።

21. ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤ጒልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።

22. ሊይዙኝ ጒድጓድ ስለ ቈፈሩ፣ለእግሮቼም በስውር ወጥመድ ስለ ዘረጉ፣በድንገት ወራሪ ስታመጣባቸው፣ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።

23. አንተ ግን እግዚአብሔር ሆይ፤ሊገድሉኝ ያሴሩብኝን ሴራ ሁሉ ታውቃለህ፤በደላቸውን ይቅር አትበል፤ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤በፊትህ ወድቀው የተጣሉ ይሁኑ፤በቍጣህም ጊዜ አትማራቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 18