ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 18:15-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ሕዝቤ ግን ረስቶኛል፤ለማይረቡ ነገሮች ዐጥኖአል፣በራሱ መንገድ፣በቀደሞው ጐዳና ተሰናክሎአል፤በሻካራው መሄጃ፣ባልቀናውም ጥርጊያ መንገድ ሄዶአል።

16. ምድራቸው ባድማ፣ለዘላለም መሣለቂያ ይሆናል፤በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤በመገረምም ራሱን ይነቀንቃል።

17. ከምሥራቅ እንደሚወጣ ነፋስ፣በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ፤በመጥፊያቸው ቀን፣ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”

18. እነርሱም፣ “ሕግ ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን፣ ቃልም ከነቢያት ስለማይታጣ ኑና በኤርምያስ ላይ እንማከር፤ ኑ፤ በአንደበታችን እናጥቃው፣ እርሱ የሚናገረውንም ሁሉ አንስማ” አሉ።

19. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማኝ፤ባላንጣዎቼ የሚሉትን አድምጥ።

20. የመልካም ተግባር ወሮታው ክፉ ነውን?እነርሱ ግን ጒድጓድ ቈፈሩልኝ፤ቍጣህን ከእነርሱ እንድትመልስ፣በፊትህ ቆሜ፣ስለ እነርሱ እንደ ተናገርሁ አስብ።

21. ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤ጒልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።

22. ሊይዙኝ ጒድጓድ ስለ ቈፈሩ፣ለእግሮቼም በስውር ወጥመድ ስለ ዘረጉ፣በድንገት ወራሪ ስታመጣባቸው፣ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 18