ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 11:14-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. “በተጨነቁ ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና አንተም ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፤ ልመና አታቅርብ፤ አትማጠን።

15. “ወዳጄ፣ ከብዙዎች ጋር ተንኰሏን እየሸረበች፣በቤቴ ውስጥ ምን ጒዳይ አላት?ስእለት ወይም የመሥዋዕት ሥጋ ቅጣትሽን ሊያስቀርልሽ ይችላልን?እነዚህንስ በመፈጸም፣ ደስተኛ መሆንትችያለሽን?”

16. እግዚአብሔር፣ ‘የተዋበ ፍሬ ያላት፣የለመለመች የወይራ ዛፍ’ ብሎሽ ነበር፤አሁን ግን በታላቅ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ፣እሳት ያነድባታል፤ቅርንጫፎቿ ይሰባበራሉ።

17. የእስራኤልና የያዕቆብ ቤት ለበኣል በማጠን ባደረጉት ክፋት ስላስቈጡኝ፣ አንቺን የተከለሽ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉ ነገር ዐውጆብሻል።

18. እግዚአብሔር ስውር ዕቅዳቸውን ገለጠልኝ፤ እኔም ዐወቅሁ፤ በዚያን ጊዜ ሥራቸውን አሳይቶኝ ነበርና።

19. እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣“ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ፤ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ።”ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።

20. ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣በጽድቅም የምትፈርድ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ጒዳዬን ላንተ ትቻለሁና፤በእነርሱ ላይ የምትፈጽመውን በቀል ልይ።

21. “እንግዲህ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹና፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር፤ አለዚያ በእጃችን ትሞታለህ’ ለሚሉህ ለዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 11