ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 4:11-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ብርቱው አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፤የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።

12. “ቃል በምስጢር መጣልኝ፤ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች።

13. በሚያስጨንቅ የሌሊት ሕልም ውስጥ፣ከባድ እንቅልፍም በሰዎች ላይ በወደቀ ጊዜ፣

14. ፍርሀትና መንቀጥቀጥ ያዘኝ፤ዐጥንቶቼም ሁሉ ተናወጡ።

15. መንፈስ ሽው ብሎ በፊቴ አለፈ፤የገላዬም ጠጒር ቆመ።

16. እርሱም ቆመ፣ምን እንደሆነ ግን መለየት አልቻልሁም፤አንድ ቅርጽ በዐይኔ ፊት ነበረ፤በእርጭታ ውስጥ እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤

17. ‘ሥጋ ለባሽ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን?ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹሕ ሊሆን ይችላልን?

18. እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ ላይ እምነት ካልጣለ፣መላእክቱንም በስሕተታቸው ከወቀሰ፤

19. ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፣መሠረታቸው ከዐፈር የሆነ፣ከብልም ይልቅ በቀላሉ የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ?

20. በንጋትና በምሽት መካከል ይደቃሉ፤ሳይታሰብም ለዘላለም ይጠፋሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 4