ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 4:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ቴማናዊው ኤልፋዝም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር፣ ቅር ይልሃልን?ዳሩ ግን ከመናገር ማን ሊቈጠብ ይችላል?

3. እነሆ፤ አንተ ብዙዎችን ታስተምር እንደ ነበር አስብ፤የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፤

4. ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤የሚብረከረከውንም ጒልበት ታጸና ነበር።

5. አሁን ግን መከራ አገኘህ፣ አንተም ተስፋ ቈረጥህ፤ሸነቈጠህ፤ ደነገጥህም።

6. እግዚአብሔርን መፍራት መታመኛህ፣ቀና አካሄድህም ተስፋህ አይደለምን?

7. “አሁንም አስተውል፤ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ፣ ማን ነው?ቅኖችስ መች ተደምስሰው ያውቃሉ?

8. እኔ እንዳየሁ፣ ክፋትን የሚያርሱ፣መከራንም የሚዘሩ ያንኑ ያጭዳሉ።

9. በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ።

10. አንበሳ ያገሣል፤ ቍጡውም አንበሳ ይጮኻል፤የደቦል አንበሳው ጥርስ ግን ተሰብሮአል።

11. ብርቱው አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፤የአንበሳዪቱም ግልገሎች ይበተናሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 4