ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:7-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ይህም የሆነው የንጋት ከዋክብት በዘመሩበት ጊዜ፣መላእክትም እልል ባሉበት ጊዜ ነበር።

8. “ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣በር የዘጋበት ማን ነው?

9. ደመናውን ልብሱ፣ጨለማንም መጠቅለያው አደረግሁለት፣

10. ድንበር ወሰንሁለት፤መዝጊያና መወርወሪያውን አበጀሁለት።

11. ‘እስከዚህ ድረስ ትመጣለህ፤ ማለፍ ግን አትችልም፤የዕቡይ ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ አልሁት።

12. “ከተወለድህ ጀምሮ ንጋትን አዘህ ታውቃለህን?ወይስ ወጋገን ስፍራውን እንዲይዝ አድርገሃል?

13. በዚህም የምድርን ዳርቻ ይዞ፣ክፉዎችን ከላይዋ እንዲያራግፍ አድርገሃልን?

14. ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ቅርጿ ይወጣል፤ቅርጿ እንደ ልብስ ቅርጽ ጐልቶ ይታያል።

15. ክፉዎች ብርሃናቸውን ተከልክለዋል፤ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሮአል።

16. “ወደ ባሕር ምንጭ ወርደህ ታውቃለህን?ወይስ ወደ ጥልቀቱ ገብተህ በመሠረቱ ላይ ተመላልሰሃልን?

17. የሞት ደጆች ተገልጠውልሃልን?የሞትንስ ጥላ በሮች አይተሃልን?

18. የምድርን ስፋት ታውቃለህን?ይህን ሁሉ ዐውቀህ ከሆነ፣ ንገረኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38