ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:34-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. “ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን?

35. መብረቆችን መስደድ ትችላለህ?እነርሱስ፣ ‘እነሆ፤ እዚህ አለን’ ይሉሃል?

36. ለልብ ጥበብን፣ለአእምሮም ማስተዋልን የሰጠ ማን ነው?

37. ትቢያ ሲጠጥር፣ጓሎችም እርስ በርስ ሲጣበቁ፣

38. ደመናትን ለመቍጠር ጥበብ ያለው ማን ነው?የሰማያትንስ የውሃ ገንቦ ዘንበል ማድረግ ማን ይችላል?

39. “ለአንበሳዪቱ አድነህ ግዳይ ታመጣለህን?የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችንስ ታጠግባለህን?

40. እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤በደን ውስጥም ይጋደማሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38