ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:32-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. ማዛሮት የተባለውን የክዋክብት ክምችት በወቅቱ ልታወጣ፣ወይም ድብ የተባለውን ኮከብና ልጆቹን ልትመራ ትችላለህ?

33. የሰማያትን ሥርዐት ታውቃለህ?ይህንስ በምድር ላይ እንዲሠለጥን ማድረግ ትችላለህ?

34. “ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን?

35. መብረቆችን መስደድ ትችላለህ?እነርሱስ፣ ‘እነሆ፤ እዚህ አለን’ ይሉሃል?

36. ለልብ ጥበብን፣ለአእምሮም ማስተዋልን የሰጠ ማን ነው?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38