ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ ልጠይቅህ፣አንተም መልስልኝ።

4. “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።

5. ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ?በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?

6. መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ?የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?

7. ይህም የሆነው የንጋት ከዋክብት በዘመሩበት ጊዜ፣መላእክትም እልል ባሉበት ጊዜ ነበር።

8. “ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣በር የዘጋበት ማን ነው?

9. ደመናውን ልብሱ፣ጨለማንም መጠቅለያው አደረግሁለት፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38