ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:27-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ባድማውንና በረሓውን መሬት የሚያጠግብ፣ሣርም እንዲበቅልበት የሚያደርግ ማን ነው?

28. ዝናብ አባት አለውን?የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው?

29. በረዶ ከማን ማሕፀን ይወጣል?የሰማዩንስ ዐመዳይ ማን ይወልዳል?

30. ውሆች እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤የጥልቁ ገጽ እንደ በረዶ ይጋገራል።

31. “ፕልያዲስ የተባሉትን ውብ ከዋክብት ልትለጒም፣ወይም የኦርዮንን ማሰሪያ ልትፈታ ትችላለህን?

32. ማዛሮት የተባለውን የክዋክብት ክምችት በወቅቱ ልታወጣ፣ወይም ድብ የተባለውን ኮከብና ልጆቹን ልትመራ ትችላለህ?

33. የሰማያትን ሥርዐት ታውቃለህ?ይህንስ በምድር ላይ እንዲሠለጥን ማድረግ ትችላለህ?

34. “ድምፅህን ወደ ደመናት አንሥተህ፣ራስህን በጐርፍ ማጥለቅለቅ ትችላለህን?

35. መብረቆችን መስደድ ትችላለህ?እነርሱስ፣ ‘እነሆ፤ እዚህ አለን’ ይሉሃል?

36. ለልብ ጥበብን፣ለአእምሮም ማስተዋልን የሰጠ ማን ነው?

37. ትቢያ ሲጠጥር፣ጓሎችም እርስ በርስ ሲጣበቁ፣

38. ደመናትን ለመቍጠር ጥበብ ያለው ማን ነው?የሰማያትንስ የውሃ ገንቦ ዘንበል ማድረግ ማን ይችላል?

39. “ለአንበሳዪቱ አድነህ ግዳይ ታመጣለህን?የተራቡ የአንበሳ ግልገሎችንስ ታጠግባለህን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38