ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:13-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. በዚህም የምድርን ዳርቻ ይዞ፣ክፉዎችን ከላይዋ እንዲያራግፍ አድርገሃልን?

14. ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ቅርጿ ይወጣል፤ቅርጿ እንደ ልብስ ቅርጽ ጐልቶ ይታያል።

15. ክፉዎች ብርሃናቸውን ተከልክለዋል፤ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሮአል።

16. “ወደ ባሕር ምንጭ ወርደህ ታውቃለህን?ወይስ ወደ ጥልቀቱ ገብተህ በመሠረቱ ላይ ተመላልሰሃልን?

17. የሞት ደጆች ተገልጠውልሃልን?የሞትንስ ጥላ በሮች አይተሃልን?

18. የምድርን ስፋት ታውቃለህን?ይህን ሁሉ ዐውቀህ ከሆነ፣ ንገረኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38