ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:12-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. “ከተወለድህ ጀምሮ ንጋትን አዘህ ታውቃለህን?ወይስ ወጋገን ስፍራውን እንዲይዝ አድርገሃል?

13. በዚህም የምድርን ዳርቻ ይዞ፣ክፉዎችን ከላይዋ እንዲያራግፍ አድርገሃልን?

14. ምድር ከማኅተም በታች እንዳለ የሸክላ ጭቃ ቅርጿ ይወጣል፤ቅርጿ እንደ ልብስ ቅርጽ ጐልቶ ይታያል።

15. ክፉዎች ብርሃናቸውን ተከልክለዋል፤ከፍ ያለው ክንዳቸውም ተሰብሮአል።

16. “ወደ ባሕር ምንጭ ወርደህ ታውቃለህን?ወይስ ወደ ጥልቀቱ ገብተህ በመሠረቱ ላይ ተመላልሰሃልን?

17. የሞት ደጆች ተገልጠውልሃልን?የሞትንስ ጥላ በሮች አይተሃልን?

18. የምድርን ስፋት ታውቃለህን?ይህን ሁሉ ዐውቀህ ከሆነ፣ ንገረኝ።

19. “ወደ ብርሃን መኖሪያ የሚያደርሰው መንገድ የትኛው ነው?የጨለማ መኖሪያስ ወዴት ነው?

20. ወደ ማደሪያቸው ልትወስዳቸው ትችላለህን?የመኖሪያቸውን መንገድ ታውቃለህ?

21. ያን ጊዜ ተወልደሃል! ዕድሜህ ትልቅ ነውና፣አንተስ በእርግጥ ሳታውቅ አትቀርም!

22. “ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃልን?የዐመዳዩንስ ማከማቻ አይተሃልን?

23. ይኸውም ለመከራ ጊዜ፣ለጦርነትና ለውጊያ ቀን ያስቀመጥሁት ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38