ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 38:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤

2. “ዕውቀት በጐደለው ቃል፣ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማን ነው?

3. እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤እኔ ልጠይቅህ፣አንተም መልስልኝ።

4. “ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ?በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።

5. ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ?በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?

6. መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ?የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?

7. ይህም የሆነው የንጋት ከዋክብት በዘመሩበት ጊዜ፣መላእክትም እልል ባሉበት ጊዜ ነበር።

8. “ባሕር ከማሕፀን በወጣ ጊዜ፣በር የዘጋበት ማን ነው?

9. ደመናውን ልብሱ፣ጨለማንም መጠቅለያው አደረግሁለት፣

10. ድንበር ወሰንሁለት፤መዝጊያና መወርወሪያውን አበጀሁለት።

11. ‘እስከዚህ ድረስ ትመጣለህ፤ ማለፍ ግን አትችልም፤የዕቡይ ማዕበልህም ገደብ ይህ ነው’ አልሁት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 38