ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 37:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ዐውሎ ነፋስ ከማደሪያው፣ብርድም ከብርቱ ነፋስ ይወጣል።

10. የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።

11. ደመናትን ርጥበት ያሸክማቸዋል፤መብረቁንም በውስጣቸው ይበትናል።

12. ያዘዘውን ለመፈጸም፣እርሱ በሚሰጠው መመሪያ፣በመላው የምድር ገጽ ላይ ይሽከረከራሉ።

13. ሰዎችን ለመቅጣት ደመና ያመጣል፤ወይም በዚሁ ምድሩን አጠጥቶ ፍቅሩን ይገልጻል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 37