ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 37:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እርሱ የፈጠራቸው ሰዎች ሁሉ ሥራውን ያውቁ ዘንድ፣እያንዳንዱ ሰው እንዳይሠራ ይገታዋል።

8. እንስሳት ይጠለላሉ፤በየዋሻቸውም ይቈያሉ።

9. ዐውሎ ነፋስ ከማደሪያው፣ብርድም ከብርቱ ነፋስ ይወጣል።

10. የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ያስገኛል፤ሰፋፊ ውሆች ግግር በረዶ ይሆናሉ።

11. ደመናትን ርጥበት ያሸክማቸዋል፤መብረቁንም በውስጣቸው ይበትናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 37