ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 37:21-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. እንግዲህ ነፋስ ሰማያትን ካጠራ በኋላ፣እጅግ የምታበራዋን ፀሓይ፣ሊመለከት የሚችል የለም።

22. እንደ ወርቅ በሚያበራ ክብር ከሰሜን ይወጣል፤እግዚአብሔር በሚያስፈራ ግርማ ይመጣል።

23. ሁሉን የሚችል አምላክ ከአእምሯችን በላይ ነው፤ በኀይልና በፍርድ ታላቅ ነው፣ጽድቁም ብዙ ነው፤ ማንንም አይጨቍንም።

24. ስለዚህ፣ ሰዎች ይፈሩታል፤በልባቸው አስተዋዮች እንደሆኑ የሚያስቡትን አይመለከትም?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 37