ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 37:16-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን፣ የእርሱን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን?

17. ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ባለች ጊዜ፣ከሙቀት የተነሣ በልብስህ ውስጥ የምትዝለፈለፍ ሆይ፤

18. ከቀለጠ ናስ እንደ ተሠራ መስተዋት የጠነከረውን ሰማይ ሲዘረጋ፣አብረኸው መዘርጋት ትችል ነበርን?

19. “ከጨለማችን የተነሣ እኛ ጒዳያችንን መግለጽ አንችልም፤ለእርሱ የምንለውን ንገረን።

20. እኔ መናገር እንደ ፈለግሁ ሊነገረው ይገባልን?ይዋጥ ዘንድ የሚጠይቅ ሰው አለን?

21. እንግዲህ ነፋስ ሰማያትን ካጠራ በኋላ፣እጅግ የምታበራዋን ፀሓይ፣ሊመለከት የሚችል የለም።

22. እንደ ወርቅ በሚያበራ ክብር ከሰሜን ይወጣል፤እግዚአብሔር በሚያስፈራ ግርማ ይመጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 37