ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 37:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እግዚአብሔር ደመናትን እንዴት እንደሚቈጣጠር፣መብረቁንም እንዴት እንደሚያባርቅ ታውቃለህን?

16. ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን፣ የእርሱን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን?

17. ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ባለች ጊዜ፣ከሙቀት የተነሣ በልብስህ ውስጥ የምትዝለፈለፍ ሆይ፤

18. ከቀለጠ ናስ እንደ ተሠራ መስተዋት የጠነከረውን ሰማይ ሲዘረጋ፣አብረኸው መዘርጋት ትችል ነበርን?

19. “ከጨለማችን የተነሣ እኛ ጒዳያችንን መግለጽ አንችልም፤ለእርሱ የምንለውን ንገረን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 37