ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 37:11-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ደመናትን ርጥበት ያሸክማቸዋል፤መብረቁንም በውስጣቸው ይበትናል።

12. ያዘዘውን ለመፈጸም፣እርሱ በሚሰጠው መመሪያ፣በመላው የምድር ገጽ ላይ ይሽከረከራሉ።

13. ሰዎችን ለመቅጣት ደመና ያመጣል፤ወይም በዚሁ ምድሩን አጠጥቶ ፍቅሩን ይገልጻል።

14. “ኢዮብ ሆይ፤ ይህን ስማ፤ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ።

15. እግዚአብሔር ደመናትን እንዴት እንደሚቈጣጠር፣መብረቁንም እንዴት እንደሚያባርቅ ታውቃለህን?

16. ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን፣ የእርሱን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን?

17. ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ባለች ጊዜ፣ከሙቀት የተነሣ በልብስህ ውስጥ የምትዝለፈለፍ ሆይ፤

18. ከቀለጠ ናስ እንደ ተሠራ መስተዋት የጠነከረውን ሰማይ ሲዘረጋ፣አብረኸው መዘርጋት ትችል ነበርን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 37