ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 34:19-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ሁሉም የእጁ ሥራ ስለሆኑ፣እርሱ ለገዦች አያደላም፤ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።

20. እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።

21. “ዐይኖቹ የሰውን አካሄድ ይመለከታሉ፤ርምጃውንም ሁሉ ይከታተላሉ።

22. ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት፣ጨለማ ስፍራ ወይም የሞት ጥላ የለም።

23. ሰው ለፍርድ ፊቱ ይቀርብ ዘንድ፣እግዚአብሔር ቀጠሮ አይዝለትም።

24. ያለ ምንም ጥያቄ ኀያላንን ያንኰታኵታል፤ሌሎችንም በቦታቸው ይሾማል።

25. እርሱ ሥራቸውን ሁሉ ስለሚያውቅ፣በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤እነርሱም ይደቃሉ።

26. ስለ ክፋታቸውም፣በሰው ሁሉ ፊት ይቀጣቸዋል፤

27. እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፤መንገዱንም ችላ ብለዋል።

28. የድኾች ልቅሶ ወደ እርሱ እንዲደርስ ሰበብ ሆኑ፤የመከረኞችን ጩኽት ሰማ።

29. እርሱ ዝም ቢል፣ ማን ሊወቅሰው ይችላል?ፊቱንስ ቢሰውር፣ ማን ሊያየው ይችላል?እርሱ ከሰውም፣ ከሕዝብም በላይ ነው፤

30. ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።

31. “ሰው ለእግዚአብሔር እንዲህ ቢል፣ የተሻለ ነበር፤‘እኔ በደለኛ ነኝ፤ ከእንግዲህ ግን አልበድልም፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 34