ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 33:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ‘ኀጢአት የሌለብኝ ንጹሕ ነኝ፤ከበደል ነጻ ነኝ፤ እድፈትም የለብኝም፤

10. እግዚአብሔር ግን ሰበብ ፈልጎብኛል፤እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል፤

11. እግሬን በግንድ አጣብቆአል፤እንቅስቃሴዬንም ሁሉ ይከታተላል።’

12. “ነገር ግን እግዚአብሔር ከሰው ስለሚበልጥ፣ትክክል እንዳልሆንህ እነግርሃለሁ።

13. የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ለምን ታማርርበታለህ?

14. ሰው ባያስተውለውም፣እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፤

15. ሰዎች ዐልጋቸው ላይ ተኝተው ሳሉ፣ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅባቸው፣በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ፣ ይናገራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 33